Value Added Tax (VAT)

User Rating:  / 3
PoorBest 

 

ተጨማሪ እሴት ታክስ

 የተጨማሪ እሴት ታክስ ዕድገትና ባህሪ

በዓለማችን የታክስ ሥርዓቶች ውስጥ ከታዩ ዕድገቶች መካከል የተጨማሪ እሴት ታክስ ዋነኛው ሲሆን ከአርባ ዓመታት በፊት በዓለማችን በጥቂት አካባቢዎች ብቻ ይታወቅ የነበረው ተጨማሪ እሴት ታክስ በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን ከሚገኙ 194 አገሮች ውስጥ በ126 ሀገሮች ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ የታክሱ መጣኔ (Tax rate)በተለያዩ አገሮች የተለያየ እና በአንዳንድ አገሮች ለተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶች በርካታ የታክስ መጣኔ ያለው ሲሆን በሌሎች አገሮች ዜሮና መደበኛ በመባል የሚታወቅ መጣኔ አለው፡፡ በርካታ የታክስ መጣኔ ያላቸው ሀገሮች የዚያን ያህል የታክሱ አስተዳደሩም የተወሳሰበ ነው፡፡ በምዕራብ አውሮፓ፣ በሽግግር ኢኮኖሚ ላይ በሚገኙ እና በአንደንድ ታዳጊ አገሮች ከፍተኛው መጣኔ እስከ 25 በመቶ ይደርሳል፡፡

 በሀገራችንም ይህ ታክስ ተግባራዊ መደረግ የተጀመረው በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በታህሣሥ 23/1994 ዓ.ም ጸደቀው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን ተከትሎ ነው፡፡ ታክሱ ገና በማደግ ላይ ያለ ቢሆንም ታክሱ  ቀደም ሲል የነበረውን የሽያጭ ታክስ ተክቶ ተግባራዊ እየተደረገ ያለ ሲሆን ልዩ የሚያደርገው በኮምፒዩተር የታገዘ እና በማምረት፣ በማከፋፈልና በስርጭት ሂደት ውስጥ በሚፈጠረው እሴት ላይ ብቻ ታክሱ የሚታሰብ መሆኑ እንዲሁም ዘመናዊና በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ የተመሠረተ የታክስ አሰባሰብ ዘዴ መሆኑ ነው፡፡ ታክሱ በየደረጃው በሚፈጠሩ እሴቶችና በፍጆታ ላይ የሚጣል ቢሆንም በየደረጃው የሚከፈለው ታክስ በተቀናሽ አስተዳደር የሚመራ በመሆኑ በምርት ሽግግር ወቅት የሚከፈለው ታክስ እንደ ዋጋ የማይቆጠር በመሆኑ ታክስ ላይ ታክስ መክፈልን ያስቀራል፡፡ ቀደም ሲል ከነበረው ግብይት ላይ የተከፈለው ታክስ ከምርት ግብይት ላይ ተቀናሽ የሚደረግ በመሆኑ የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች የምርታቸውን ዋጋ ሲተምኑ ከአጠቃላይ የማምረቻ/ምርቱን ለማግኘት ባወጡት ዋጋ ላይ ሳይደምሩ ይተምናሉ፡፡ በግብይቱ ሂደት የከፈሉትንም በዋጋ ውስጥ አካተው ከተመኑ የምርቱ መሽጫ ዋጋ እንዲወደድ ያደርጉታል፡፡ የደንበኞችንም መሸሽ ያስከትላሉ፡፡  

የሀገራችን የተጨማሪ እሴት ታክስ ባህሪ

የተጨማሪ እሴት ታክስ በምርት ማምረት፣ በማከፋፈልና በስርጭት ሂደት ውስጥ በየደረጃው በሚፈጠረው እሴት እና በአገልግሎት ወቅት በተጨመረው እሴት ላይ የሚጣል ታክስ ነው፡፡ ምርት ተመርቶ ከመሸጡ በፊት በሚኖረው ሂደት በግብይት ወቅት የተከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ምርቱ ከመሸጡ በፊት በግብዓት ላይ የተከፈለ ታክስ በምርት ሽያጭ ላይ ከሚሰበሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ተቀናሽ የሚደረግበት አሠራር ያለው በመሆኑ ቀደም ሲል ከነበሩ የሽያጭ ታክሶች ላይ ይታዩ የነበረውን የታክስ ተደራራቢነት የሚያስቀር ነው፡፡ ታክሱ በግብይት ሂደት በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት ላይ የሚከፈል በመሆኑ ለልማት በቂ ገቢ ከማስገኘት አኳያ መሰረተ ሰፊ የሆነ ታክስ ነው፡፡¬Ks# bGBYT £dT bFí¬ X”ãC xgLGlÖT §Y y¸kfL s!çN bµpE¬L :”ãC §Y ytkflN ¬KS tm§> y¸ÃdRG bmçn#x!NvSTmNTN Ãb‰¬¬LÝÝ

 ታክሱ በደረሰኝ ላይ የተመሠረተ የማቀናነስ መንገድ ይከተላል፡፡ ታክስ ከፋዩ ዕቃዎችን/አገልግሎቶችን ሲገዛ ለከፈለው ታክስ እና ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ሲሸጥ ለሚቀበለው ታክስ ደረሰኝ በመሰብሰብና በመያዝ አቀናንሶ በተጨማሪ እሴት ላይ የሰበሰበውን ታክስ ለመንግሥት ገቢ የሚያደርግበት ሥርዓት የሚከተል ነው፡፡ ለዚህም ታክስ ከፋዩን በየጊዜው ደረሰኞችን መሰብሰብና መያዝ የሚጠይቅ ነው፡፡

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.