Turn Over Tax (TOT)

User Rating:  / 1
PoorBest 

የተርን ኦvር ታክስ ዋና ዋና ገጽታዎች

መግቢያ

በአገራችን የታክስ አስተዳደር ስርዓት ውስጥ ሁለት ዓይነት የታክስ አወቃቀር(ምድቦች) ያሉ ሲሆን እነዚህምቀጥታ ታክስ እናቀጥታ ያልሆነ ታክስበመባል ይታወቃሉ፡፡ቀጥታክስ ማንኛዉም ሰዉ በሚያገኘዉ ገቢ ወይም ያዘዉ ሀብትጋር በተያያዘ በቀጥታ ባገኘዉ ኢኮኖሚያዊጥቅም ላይ በታክስ ሥርዓቱ በተደነገገዉ ጣኔ መሠረት የሚጣል ታክስ/የግብር ዓይነት ሲሆንታክቀጥተኛ ከፋይ ገቢዉን/ጥቅሙንያገኘዉ ሰው/ድርጅት በመሆኑ ግዴታውን ወደ ሌላዉ አካልፍፁም ሸጋገር ፡፡ በቀጥታ ታክስ ስር ሚመደቡ የመንግስት የገቢግብር ዓይነቶችውስጥ  ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ ላይ የሚከፈል ግብርየቤት ኪራይ ገቢ ግብርእና የንግድ ሥራ ትርፍ ግብርዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ቀጥታ ያልሆነ ታክስ ግብር ከፋዩ በታክስ ህጉ መሠረት ከመንግስት ባገኘው ውክልና በሚሸጠዉ ዕቃ/ አገልግሎት ላይ በማሰብ የሚሰበሰበዉና ለመንግስት ገቢ የሚያደርገዉ የታክስ ዓይነት ነዉ፡፡ ይህ ታክስ በቀጥታ የሻጩን/አገልግሎት ሰጪውን ጥቅም የማይነካና በቀላሉ ወደ ተጠቃሚዎች የሚሸጋገር በመሆኑትክክለኛው የታክሱ ከፋዮች ሸማቾች ወይም ተጠቃሚዎች  ናቸው፡፡በዚህ ምድብ ከሚካተቱ የታክስ ዓይነቶች ውስጥ አንዱ የተርን ኦvር ታክስ ሲሆን ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከተመዘገቡ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች ውጭ ይህንን ታክስ የሚያካትት ግብይት የሚያካሄዱ የደረጃ “ለ” እና “ሐ” ግብር ከፋዮች በሙሉ ታክሱን ከተጠቃሚው በመሰብሰብ ለመንግስት ገቢ የማድረግ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡

የ2004 ዓ.ም መረጃ እንደሚያመለክተው በክልላችን ከሚገኙ 127000 ያህል  የንግድ ዘርፍ ግብር ከፋዮች ውስጥ ከ123000 (97%) በላይ የሚሆኑት የደረጃ “ለ” እና “ሐ” ግብር ከፋዮች በመሆናቸው የተርን ኦvር ታክስ ጉዳይ ይመለከታቸዋል፡፡በመሆኑም እነዚህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግብር ከፋዮች ስለታክሱ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሳድጉ ማድረግ ያለውን የጎላ ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ  በተርን ኦvር ታክስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ጽሁፍ እንዲዘጋጅ ተደርÙ፡፡

 ተርን ኦቨር ታክስ  ምንድን ነው?

ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ላይ የሚከፈል ታክስ ነው፡፡ ታክሱ በየደረጃው በሚገኙ የምርት ሂደቶች/ማምረት፣ ማከፋፈልና ስርጭት...ወዘተ ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ አካል ነው፡፡ ተርን ኦቨር ታክስ  ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ እንደ መሆኑ መጠን የታክሱ ቀጥታ ከፋዮች ተጠቃሚዎች ወይም ሸማቾች ናቸው፡፡ ታክሱ የሚሰበሰበው ከሸማቹ/ከተጠቃሚው በመሆኑ ከግብር ከፋዩ ንግድ ትርፍና ኪሳራ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነትየለውም፡፡ 

የተርን ኦv ታክስ በንግድ ግንኙነት ውስጥ ፍትሃዊነትን ለማስፈን ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ግብር ከፋዮች ግዴታቸውን እንዲወጡ የማሰተካከያ/የማካካሻ ታክስ መጣል በማስፈለጉ እንዲሁም የታክስ ርዓቱን ሽፋን የተሟላ በማድረግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ሲባል በአዋጅ የተጣለ የታክስ ዓይነት ነው፡፡

በመሆኑም ተርን ኦቨር ታክስ ከብር 500 ሺ በታች የሆነ አመታዊ የንግድ እንቅስቀሴ ያለው ማንኛውም ሰው/ድርጅት የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ ከሸማቹ ሰብስቦ ለታክስ ባለስልጣኑ ገቢ የሚያደርገው የታክስ አይነት ነው፡፡

ተርን ኦቨር ታክስ ለመሠረተ ልማት ግንባታ እና ለሌሎችም በመንግስት ለሚታቀዱ የተለያዩ ሥራዎች ማስኬጃ የሚደለደለውን ገንዘብ ለማመንጨት በመሣሪያነት ከሚያለግሉት ውጤታማ የታክስ ዓይነቶች አንዱ በመሆንም ይታወቃል፡፡

የተርን ኦቨር ታክስ ተመን (ምጣኔ) ምን ያህል ነው እንዴትስ ይሰላል?

ytRN åvR ¬KS l¥S§T msrT y¸çnW yX”W wYM yxgLGlÖt$ -Q§§ y>Ã+ gb! ነው፡፡ ከተሸጠ ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚሰበሰበው የተርን ኦቨር ታክስ የሚሰላው ጠቅላላ የሽያጭ ገቢና የማስከፈያ ልክ (rate) በማባዛት ይሆናል፡፡ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ማለት የወጪ ተቀናሽ ሳይደረግ የተገኘ ጠቅላላ ገቢ ሲሆን የተሸጡት ዕቃዎች የተመረቱበትን ወይም የተገዙበትን ዋጋ  ይጨምራል፡፡ በዚህ መሠረት በማናቸውም በአገር ውስጥ በሚሸጡ እቃዎች 2 /ሁለት በመቶ/ ተርን ኦቨር ታክስ የሚከፈል ሲሆን ለምሳሌ አንድን እቃ በብር 500 የሸጠ ማንኛውም ሰው/ድርጅት ከሸማቹ የሚሰበሰበው ተርን ኦቨር ታክስ 500 x 2/100 =10 ብር  ይሆናል ማለት ነው፡፡

የአገልግሎት ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ተከፋዩን ተርን ኦቨር ታክስ ለማስላት የምንጠቀምበት ምጣኔ በተሸጠው ወይም ለሸማቹ በተሰጠው የአገልግሎት ዓይነት ይወሰናል፡፡ ለምሳሌ ሥራ ተቋራጮች፣ የእህል ወፍጮ ቤቶች፣ ትራክተሮች እና የኮምባይን ሀርቨስተሮች በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የሚከፈለውን ተርን ኦቨር ታክስ ለማስላት የሚያለግለው ምጣኔ 2%  ሲሆን በሌሎች አገልግሎቶች ግብይት ወቅት 10% (አስር በመቶ) ተርን ኦቨር ታክስ ይከፈላል፡፡

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.