Rental Income Tax

User Rating:  / 2
PoorBest 

ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ ስለማስታወቅ እና ግብር ስለመከፈል

በማናቸውም ሁኔታ ከተከራየ ቤት በሚገኝ ገቢ ላይ  አንድ ግብር ከፋይ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ከንግድ ሥራ የተለየ ሂሳብ መዝገብ ይዞ ግብሩን መክፈል አለበት፡፡ ግብር ከፋዩ በያዘው የሂሳብ መዝገብ መሠረት ከቤት/ህንፃ ከማከራየት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸዉን በመረጃ የተደገፉትን ወጪዎች/ ለምሳሌ፦ ገቢን ለማስገኘት፣ ለማስቀጠልና ዋስትና ለማሰጠት ያወጣቸዉ/ ሁሉ ተቀናንሰዉ በሚገኘዉ የተጣራ ትርፍ ላይ የሚፈለግበትን ግብር አስልቶ በግብር ማስታወቂያ ጊዜ ውስጥ ማስታወቅ አለበት፡፡ ምናልባት ግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ ይዞ ባይገኝ የሚፈለግበትን ግብር የግብር ባለሥልጣኑ በግምት ይወስንበታል፡፡

የግብር ባለሥልጣኑም ግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ የኪራይ ገቢ ላይ ለመድረስ ተቀናሽ ወጪዎችን ፤ማለትም የመሬትና የሕንፃ /የቦታ/ ግብር እና አንድ አምስተኛ /20 በመቶ /የጠቅላላ የቤቱ ወይም የመሣሪያ ገቢ ለቤት ዕቃና ለመሣሪያ ማደሻ፣ መጠገኛና ለእርጅና መተኪያ የወጣ ወጪ እንደሆነ በማሰብ  ከጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ተቀናሽ ያደርጋል፡፡

 

ከዚህ የሚገኘዉን ወጤት የግብር ከፋዩ የተጣራ ትርፍ እንደሆነ አድርጎ የተጣራ ትርፉ/ ግብር የሚከፈልበት ገቢው የሚያርፍበት ምጣኔ በማባዛት የሚከፈለውን ግብር ለይቶ የታክስ ማስታወቂያ ለግብር ከፋዩ ይልካል፡፡

በዚህም መሰረት ከኪራይ ቤቶች በሚገኝ ገቢ ላይ የሚከፈለው ግብር የሚወሰነው የሚመደበውና የሚከፈለው ከዚህ በታች  በተመለከተው ልክ ነው፡፡

   ሀ/  በሕግ የሰውነት መብት ከተሰጣቸው ድርጅቶች ገቢ ላይ ሲሆን ግብር   ከሚከፈልበት ገቢ ላይ 30%/ ሰላሣ በመቶ፣

   ለ/  በግለሰቦች ገቢ ላይ ሲሆን  በዓመት እሰከ ብር 1800 ግብር የሚከፈልበት  የዓመት ኪራይ ገቢ ከታክስ ነፃ ሲሆን ከዚህ በላይ ገቢ የሚያገኙ ግብር ከፋዮች ከዚህ በታች በላው ሠንጠረዥ መሠረት ግብር ይከፍላሉ፡፡

 

 

ከኪራይ የሚገኝ ዓመታዊ  ገቢ

የሚከፈለው ግብር መቶኛ

ተቀናሽ

ከ0-1800 ብር

ከግብር ነፃ

-

1801-7800

10%

180

7801-16800

15%

570

16801-28200

20%

1410

28201-42600

25%

2820

42601-60000

30%

4950

ከ60000 ብር በላይ

35%

7950

 

 

 

 

 

 

 

 

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.