የግብር/ታክስ ስወራንና ማጭበርበርን በጋራ ለመከላከል የጋራ አቋም መያዝ ይገባል ተባለ::

User Rating:  / 2
PoorBest 

 

የግብር/ታክስስወራንናማጭበርበርንበጋራለመከላከልየጋራአቋምመያዝይገባልተባለበየደረጃው ከሚገኙ የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅታዊ አሰራር ላይ የጋራ የምክክር መድረክ ተዘጋጅቷል::

በገቢ ግብር አዋጁ የተሰጣቸውን በራሳቸው አሳውቀው ግብር የመክፈል መብት በመጠቀም በወቅቱ እና በአግባቡ ግብራቸውን የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች እንዳሉ ሁሉ ለታክስ ህጉ ተገዢ ባለመሆን በግብር ማጭበርበር እና ስወራ ላይ የተሰማሩ ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦች ይገኛሉ፡፡ በዚህም ለታክስ ህጉ ተገዢ ያልሆኑትን ግብር ከፋዮች በመለየት ከጥፋታቸው ታርመው ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲገቡ እና ሌሎቹም በጥፋተኞች ከተወሰደው ህጋዊ እርምጃ ትምህርት እንዲያገኙ ለማስቻል የህግ ማስከበር ስራ ተፈጻሚ እየሆነ ይገኛል፡፡ ሆኖም የህግ ማስከበሩ ስራ የግብር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ስራ ብቻ ተደርጎ የሚወሰድ ባለመሆኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ለማድረግ በክልሉ ከሚገኙ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ፣ ከስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን፣ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን፣ ከፍትህ ቢሮ እና ፍትህ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

 

የምክክር መድረኩ አላማ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር የጋራ ተልእኮ ካላቸው ተቋማት ጋር በግብር/ታክስ ህጎች ከምርመራ እሰከ ማስተዳደር ሂደት ባሉ ችግሮች ላይ በመወያየት የጋራ ግንዛቤ ለመያዝና የተቀናጀ አሰራር ስርዓት በመፍጠር የታክስ ስወራና ማጭበርበርን በመቀነስ ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ገቢን ሰብስቦ ለህዝብ ልማት እንዲውል ለማደረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በመግባባት በጋራ የኪራይ አመለካከት እና ተግባርን ለመታገል ነው፡፡

 

በውይይቱ ላይ በታክስ ማጭበርበር ሂደት በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመሰራታቸው የተገኙ ጥሩ ልምዶች የቀረቡ ሲሆን ከባለ ድርሻ አካላት አንጻር የነበሩ ክፍተቶችም ተለይተው ቀርበው  በሰፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አጎ እንደገለጹት ግለሰቦች ጥረው ለፍተው የላባቸውን ከመጠቀም ይልቅ በአቋራጭ ለመበልጸግ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት ያለ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ መነገድ፤ ኮንትሮባንድ ፣ ታክስ ማጭበርበር ፣ የመሳሰሉት ላይ መሳተፍ የተለመደ እየሆነ በመምጣቱ ሁሉም ባለድርሻ አካል ከመንግስት የተጣለበትን አደራ በመወጣት አጥፊዎችን ለፈጸሙት ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች  በበኩላቸው ግብር/ታክስ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ለልማት አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ እንደመሆኑ እነዚህ ተቋማት በጋራ ዓላማ በሀገሪቱ መልካም አስተዳደርን በማስፈንና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የግብር ስወራና ማጭበርበር ወንጀሎችን በአግባቡ ተቀናጅተው በመከላከል የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.