ወጣትና ሴቶች አደረጃጀቶች ለከፈሉት ገንዘብ ደረሰኝ እንደዲቀበሉ ግንዛቤ የመፍጠሩ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቆመ::

User Rating:  / 1
PoorBest 

 

 

በክልሉ ከሚገኙ ሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት እና በሁሉም እርከን ንቅነቄ ለመፍጠር ውይይት ተካሄደ::

በሀገራችን ተንሰራፍቶ የቆየውን ድህነትና ኋላቀርነት ለማስወገድ መንግስት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዶችን አዘጋጅቶ በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን አያሌ እምርታዊ ለውጦች ማስመዝገብ የተቻለ በመሆኑ በሂደቱ ከሚገኙ ሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች ጋር በጋራ ለመስራት ውይይት አካሂዷል፡፡

 የተገኙ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን በመቀመርም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡

በዚሁ እቅድ ላይ ያስቀመጣቸውን ግቦች እውን በማድረግ የህዝቡን የልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በብቃት እንዲመልስ ከሚያስችሉት እና ከሚያስፈልጉት ግብዓቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ገቢ /የፋይናንስ አቅርቦት ሲሆን በትራንስፎርሜሽን እቅድ  ልዩ ትኩረት የተሰጠው የስራ እድል ፈጠራ ሲሆን ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደውም ይኸ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ ከልማቱ ከሚገኘው ጥቅም ተገቢው ክፍፍል ለወጣቱ እና ለሴቶች እንዲደርስ የታክስ ስርዓቱን ከማጭበርበር የጸዳ ከሙስና የተጠበቀ እንዲሁም ፍትሀዊነቱን የጠበቀ አድርጎ ለማስቀጠል መንግስት ከሚጫወተው መንግስታዊ ሚና ጎን ለጎን የወጣቶች እና የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ይህንን ሚና በተደራጀ እና በእውቀት መምራት እንዲቻል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ  በክልሉከሚገኙ ሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች ጋር በጋራ ለመስራት ውይይት አካሂዷል፡፡

 

የውይይቱን የመክፈቻ ስነ ስርዓቱን ያደረጉት የባለስጣልን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ዲላ እንደገለጹት በክልሉ ውስጥ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ለማሳካት የተያዙ ሰፊ የመሰረተ ልማት፤ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት ግቦችን በማሳካት በዋናነት ወጣቱ እና ሴቷ በስራ እድል ተጠቃሚ አንዲሆኑ ልማታዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት በመገንባት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን  ገቢ አሟጦ የመሰብሰብ  ተልእኮ በግምባር ቀደምትነት ተቋሙ የሚወስደው ድርሻ እንዳለ ሆኖ የአደረጃጀቶችን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በእቅድ ተይዞ በየዓመቱ ለአደረጃጀቶቹ እየተሰሩ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ያሉ ቢሆንም ከክልል ማዕከል ጀምሮ ከተፈጠረው ግንዛቤ መነሻ በማድረግ ተልእኮ ሰጥቶ ስራው የደረሰበት ደረጃ ከመገምገም አንጻር  ጉድለቶች እየታዩ  በመሆናቸው ጉድለቶቹ ላይ ተግባብቶ  በቀጣይ በቅንጅት መሰራት ያለባቸው ነገሮች ላይ መግባባት መቻል እንዳለበት  ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የ9 ወር የስራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በግምገማው ላይ በዞን እና በከተማ ያሉ አደረጃጀቶች የግብር/ታክስ ተግባርን ወደ ጎን በመተው  በሌላ ሴክተር ስራዎች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ፣ ከገቢ ባለስልጣኑ ጋር ተቀናጅቶ ከመስራት አንጻር በአንዳንድ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የተሻለ ቢሆንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ዝቅተኛ መሆኑ የተነሱ ሲሆን በቀጣይ እነዚህን ችግሮች በማስተካከል ከባለስልጣኑ ጎን መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል፡፡

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት ባለፉት 9 ወራት የተሰሩት ስራዎች ከተደራሽነት አንጻር ያለው አፈጻጸም ዝቅተኛ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ያስገነዘበ መድረክ መሆኑን ገልጸው በክልሉ የሚገኙ ወጣቶችም ሆኑ ሴቶች ግዢ ሲገዙም ሆነ አገልግሎት ሲያገኙ ለከፈሉት ገንዘብ ደረሰኝ እንዲቀበሉ ግንዛቤ የመፍጠሩ ሂደት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

 

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.