የሚፈለግባቸውን ግብር/ታክስ በጊዜ በመክፈል ከሚመጣባቸው አላስፈላጊ አስተዳደራዊ ቅጣትእና ወለድ ራሳቸውን ማዳን ይጠበቅባቸዋል ተባለ፣

User Rating:  / 1
PoorBest 

 

 

የሚፈለግባቸውንግብር/ታክስበጊዜበመክፈልከሚመጣባቸውአላስፈላጊ አስተዳደራዊ ቅጣትእና ወለድ ራሳቸውን ማዳን ይጠበቅባቸዋል ተባለ፣ የ2008 በጀት ዓመት የግብር መክፈያ ወቅትን በማስመልከት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

በክልሉ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ግብር ከፋዮች እንደየ ገቢ አቅማቸው በ3 ደረጃ የተከፈሉ ሲሆን እነሱም የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ሽያጫቸው ከብር 500‚000 በላይ፣ የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ሽያጫቸው  ከብር 100‚000- ብር 500‚000 ፣ እንዲሁም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ሽያጫቸው  እስከ ብር 100‚000 የሚደርስ ሲሆኑ ዓመታዊ የስራ እንቅስቃሴያቸውን ታሳቢ በማድረግ ግብር የሚከፍሉበትን ወቅት በግብር አዋጁ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ ግብር ከፋዮች እንደየደረጃቸው የተቀመጠላቸውን የገቢ ግብር መክፈያ ጊዜያት ጠብቀው ግብራቸውን ገቢ እንዲያደርጉ በዚሁ አዋጅ ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራተ ዲላ መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንደገለጹት በክልሉ የሚገኙ ግብር ከፋዮች  ከሀምሌ/2007 እስከ ሰኔ/2008 ድረስ ሰርተው ካገኙት ገቢ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ዓመታዊ ግብራቸውን የሚከፍሉበት ወቅት መሆኑን ገልጸው በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ የሚፈለግባቸውን ግብር በወቅቱና በአግባቡ መክፈል እንዲችሉ ባለስልጣን መ/ቤቱ ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከነዚህም መካከል ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ያለውን ክፍተት በማሻሻል እና የተቀናጀ የአንድ መዓከል አገልግሎት መስጠት የሚቻልበትና የንግዱ ማህበረሰብ ሳይጉላላ ግብሩን በአግባቡ መክፈል እንዲችል ለማድረግ በየደረጃው ካሉት ከንግዱ ማህበረሰብ አደረጃጀት አመራሮች ጋር ምክክር የተደረገ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ  ከንግድ ኢንደስትሪ ጋር በመቀናጀት ግብር ከፋዮች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ገቢ ሰብሳቢ መዋቅሩ በሚመጡበት ወቅት ግብራቸውን በአግባቡ ከከፈሉ በኋላ የንግድ ፈቃዳቸው የሚታደስላቸው መሆኑንና የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በሁሉም ማዕከላት ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ይህም ሁኔታ እንዲፈጠር ለማድረግ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በመግባባት ስራውን ለመከታተል የሚያስችል የክትትል እና ድጋፍ ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ ሲሆን ከዚህ ቀደም የነበሩትን መጉላላቶች በመቀነስ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ከሚገኙ ግብር ከፋዮች መካከል 127‚953 የሚሆኑት የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች መሆናቸውንና እነዚህም ግብር ከፋዮች የአንድ ወር የጊዜ ገደብ ብቻ እንዳላቸው ገለጸው ግብር ከፋዮቹ ባላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግብራቸውን እንዲከፍሉ በየደረጃው ባሉት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የገቢ መሰብሰቢያ ማዕከላት በከተሞች እንዲከፈት ተደርጓል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ግብር ከፋዩ የመክፈያ ወቅቱን አስቀድሞ በማወቅ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ግብር ከፋዩ የሚከፍለውን ግብር አስቀድሞ እንዲያውቅ መደረጉ እና በተለይ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ከ ሀምሌ 1 እሰከ 15 ባሉት ቀናት ውስጥ ግብራቸውን አጠናቀው በመክፈል ወደየስራቸው መመለስ እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸው የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ቅስቀሳ የተደረገ በመሆኑ ግብር ከፋዩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አመታዊ  ግብሩን በተሰጠው የጊዜ ገደብ በመክፈል  ከሚመጣበት አላስፈላጊ ቅጣት ራሱን ማዳን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ዋናዳይሬክተሩአያይዘውእየተሻሻለያለውየገቢግብርአዋጅረቂቅለቀጣይ 2009 .ተፈጻሚየሚሆንበመሆኑግብርከፋዮችበነባሩአዋጅመሰረትብራቸውን አሳውቀው መክፈል ይኖርባቸዋልብለዋል፡፡

Wednesday the 20th. . Design © Top poker sites - All rights reserved.