የ2008 ዓመታዊ የግብር አሰባሰብ ስራ በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ በተካሄደ ደማቅ ስነ ስርዓት በይፋ ተጀመረ

User Rating:  / 1
PoorBest 

 

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ እና ሌሎችም የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በእለቱ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የግብር አሰባሰብ ስራዎችን ያስጀመሩት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ እንደገለጹት በከተማው እየተሰራ ያለው ልማት የግብር ውጤት መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ የድርጅት እና የህዝብ ክንፉን በጋራ በመስራትና የተሸለ ገቢ በመሰብሰብ የከተማ ልማቱን ስራ በስፋት መስራት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

 ለዚህም የግብር አሰባሰብ ስራው በይፋ የተጀመረ በመሆኑ የከተማውን ግብር ከፋዮች በተቀመጠላችው ጊዜ ውስጥ ግብራቸውን በመክፈል ለከተማው ልማትና ለህዝቡ ተጠቃሚነት አስተዋዕጾ አንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

 የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፈቃዱ ፍስሀ በበኩላቸው ባለፉት ሶስት እና አራት ዓመታት በየዓመቱ በከተማው ነዋሪዎች ግብር በመሰብሰብ የከተማውን የልማት ወጪ በራሷ መሸፈን የቻለች ከተማ መሆኗን ገልጸው ከከተማው ከሚሰበሰበው ገቢ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ለካፒታል ፕሮጀክት የሚውል እንደሆነና ይህም የከተማውን የልማት ጥያቄ በፈጣን ሁኔታ እየመለሰ ያለመሆኑና በቀጣይ የግብር አሰባሰቡ ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

 

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ያጠቃለሉት የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ዲላ በበኩላቸው አሁን እየተሰበሰበ ያለው ገቢ ከከተማው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አንጻር ዝቅተኛ እንደሆነ መረጃዎች እንደሚያሳዩና የግብር ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ግብር ከፋዮች እንዳሉ ሁሉ ግብር የሚሰውሩ እና የሚያጭበረብሩ በመኖራቸው እንደሆነ ገልጸው በየአካባቢው ያሉ አደረጃጀቶች እነዚህን ግለሰቦች በማጋለጥ መሰብሰብ ያለበት ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋዕጾ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የገቢዎች ባለስልጣን፣ የንግድ ኢንዱስትሪ እና የብቃት አረጋጋጭ ተቋማት ተገኝተው አገልግሎታቸውን በቅንጅት መስጠት የጀመሩ ሲሆን በእለቱ በርካታ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በስፍራው ተገኝተው ዓመታዊ ግብራቸውን ከፍለዋል፡፡

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.