በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን 16.8 ቢሊዮን ብር ለመሰበስበ ታቀደ

User Rating:  / 1
PoorBest 

 

በመጀመሪያው የእገትና ትራንፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም እና በሁለተኛው የእገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ክልል አቀፍ የምክክር  ጉባኤ ተካሄደ::

  በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አመታት በተቋም ለመፈጸም ከታቀዱት የገቢ ፊዚካል እና ፋይናንሻል ግቦች ውስጥ በአብዛኛው በላቀ ሁኔታ የተፈጸሙ ሲሆን የክልሉን ገቢ አሰባሰብ በ2002 ዓ.ም 944 ሚሊዮን ከነበረበት በ2007 በጀት ዓመት 4.67 ቢሊዮን ለማድረስ ታቅዶ ገቢ ብር 5 ቢሊዮን ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ የወጪ በጀት የመሸፈን አቅሙ 18 በመቶ ከነበረበት በ2007 በጀት ዓመት 32 በመቶ ማድረስ መቻሉን ተጠቁሟል፡፡

 

በአንደኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዓመታት የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው እና በተመዘገቡ ደካማ አፈጻጸሞች ላይ ምክክር ለማድረግ ሴክቶሪያል ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የጉባኤውን መክፈቻ ያደረጉት የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻ ጉባኤው ለየት የሚያደርገው የህዳሴ ጉዞ አካል የሆነውን የአንደኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በክልልም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ በስኬታማነት በማጠናቀቅ የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን በተጀመረበት ወቅት በመሆኑ ገልጸው፣ የገቢ መሰረቱን ከማስፋት አንጻር በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻ በክልሉ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራው ግብር ከፋዮች 82,281 ከነበሩበት በ2007 ዓ.ም 170 ሺህ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ቁጥር በ2002 በጀት ዓመት መጨረሻ 985 ግብር ከፋዮች ከነበሩበት ወደ 10,893 ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው የታክስ ስርዓት ማሻሻያ /SIGTAS/ ፕሮግራም ተግባራዊ በመደረጉ በርካታ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው በትራንስፎርሜሽኑ መነሻ በክልል ማእከል ብቻ ተግባራዊ ሲደረግ ከነበረው በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ባጠቃላይ በ70 ቅ/ጽ/ቤቶች ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እና የ2007 በጀት አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዓመታት በተቋሙ ከተስተዋሉት ችግሮች መካከል የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባር፣ ትክክለኛ እና ታዓማኒነት ያለው የመረጃ አያያዝ ችግር፣ ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ያለመስጠት፣ ፍትሀዊ የግብር አወሳሰን ስርዓት ያለመኖር እና የመሳሰሉ ችግሮች  እንደነበሩ  ተጠቁሞ በቀጣይ ላሉት 5 ዓመታት የታዩትን ክፍተቶች  በመድፈን በክልሉ ለተያዘው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሳካት የተቋሙ አመራር እና ሰራተኛ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡

በተለይም የገቢ ልማት ሰራዊት በመገንባት በዘርፉ ስራዎችንም ሆነ በከተማ ልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ የበላይነትን በልማታዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ የበላይነት በመተካት የገቢ ልማት ሰራዊት የሆነውን የንቅናቄ አጀንዳ የማሳካት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶ ሊፈጸም የሚገባው ተልዕኮ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ብር 16.85 ቢሊዮን እና በ2008 በጀት ዓመት ብር 6.4 ቢሊዮን ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን እቅዱን ለማሳካት ከተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በተጨማሪ የሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላት ለእቅዱ ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጥሪ ተላልፏል፡፡

 

 

 

 

 

 

Monday the 17th. . Design © Top poker sites - All rights reserved.