ጥቆማ ምንድን ነው?

User Rating:  / 1
PoorBest 

ግብር/ታክስ መሰወርና ማጭበርበር በሀገር ላይ ሊያደርስ የሚቸለውን ጉዳት አስተውለው ያውቃሉ;እንግዲያውስ፡-

ግብር/ታክስ መሰወርና ማጭበርበር መንግስት ለልማት የሚያስፈልገውን ገቢ ያሳጣል፡፡በዚህም የተነሳ በሀገሪቱ ውስጥ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ይፈጠራል፤የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት እንዳይኖር ያደርጋል፤የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይፈጠራሉ፤ሥርዓት አልበኝነት እና ሥራ አጥነት ይስፋፋል፡፡ በአጠቃላይ  የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሽመደመድ እና የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

በሠለጠኑ  ሀገራት ዜጎች የሚጠበቅባቸውን ግብር/ታከስ በወቅቱ አሳውቀው መክፈል የዜግነት ግዴታና የስልጣኔ መገለጫ ሲሆን በሌላ በኩል ግብር/ታክስ መሰወርና ማጭበርበር አሳፋሪና የሚያስወቅስ ተግባር ከመሆኑም አልፎ በሀገር ላይ ክህደት አንደፈፀመ ተደርጎ ከማህበራዊ አገልግሎት እንደሚያገለግልና አስነዋሪ ድርጊት መሆኑ ይታመናል፡፡ይሁንጂ በሀገራችን ብሎም በክልላችን ግብር/ታክስ መሰወርና ማጭበርበር እንደ ክህሎትና ጀብድ እንደፈፀሙ ቆጥረው በኩራት የሚገለፅበት ተግባር ሆኖ ታክሱን/ግብሩን ባጭበረበሩ ግብር ከፋዮች ዘንድ ሲታይ ቆይቷል፡፡

Thursday the 21st. . Design © Top poker sites - All rights reserved.